በ2025 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ የወባ በሽታዎች እና 103 ሰዎች ሞት መመዝገቡ ተገለጸ። ይህ የወባ ወረርሽኝ በዋነኛነት በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች ላይ መከሰቱን ካፒታል ከዩኒሴፍ አዲሱ ሪፖርት ተመልክቷል።
በዚሁ ጊዜ ውስጥ በአማራ እና ጋምቤላ ክልሎች ከ4,373 በላይ የኮሌራ በሽታዎችና 42 ሰዎች ሞት መመዝገቡም ታውቋል።
በሀገሪቱ የውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር 3.3 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ አብዛኞቹ በግጭት (69%) እና በድርቅ (17%) ምክንያት የተፈናቀሉ መሆናቸውን ሪፖርቱ አሳይቷል።
ዩኒሴፍ እንዳስታወቀው በ2025 የመጀመሪያ አጋማሽ ለአምስት ዓመት በታች ለሆኑ 331,000 ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሕክምና ሰጥቷል። ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሴቶች እና ህጻናት የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ሲያገኙ፣ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክቷል።
CapitalNews
