ወላጅ እናት ወ/ሮ ሀና በየነ ትባላለች የድሬዳዋ ከተማ ገንደቆሬ ሰፈር ነዋሪ ስትሆን ከቀድሞ ባሏ ጋር የተፈታችው ይህቺ ሴት ከእሷ ጋር እየኖረ ባለው ሌላ ወንድ ከአብራኳ የወጣችውን የገዛ ሴት ልጅዋ ተገዳ መደፈሯን ስታውቅ እጮኛዋን በወንጀል እንዲቀጣ ማድረግ ሲገባት የ11 ዓመት ልጇ ላይ ፈርዳ መረጃ ለማድበስበስ በማሰብ ልጇን ላይ ጫና በመፍጠር በድብደባ አካላዊ ጉዳት ከማድረስ በተጨማሪ ከ5ተኛ ክፍል የትምህርት ገበታ እና ከጎረቤቶቿ በመነጠል ከማንም ሰው ጋር ምንም ግንኙነት እንዳታረግ በማድረግ ለብዙ ጊዜ ቤት ተዘግቶባት እና ስራ ቦታ ድረስ ከስሯ ሳትነጥላት ብትንቀሳቀስም መረጃ ለመደበቅ በቂ ሆኖ ስላላገኘችው በመጨረሻ በአብራኳ በወጣችው የገዛ ልጇ ላይ የሰራችው ተደጋጋሚ የአረመኔ ሥራ ሳያንሳት እጮኛዋን ከወንጀል ለማትረፍ መረጃ ለማጥፋት ህዳር 1 ቀን 2015 ዓም ከእጮኛዋ ጋር በመተባበር ቀጥቅጠው ህፃን በአምላክ ግርማን ገደሏት።
በወላጅ እናቷ እና እንጀራ አባቷ ሕይወቷ ያለፈው ሕፃን በአምላክ ግርማ አበጋዝ ጉዳይ ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የቅጣት ውሣኔ ሰጥቷል።በዚህም መሠረት እናቷ ሀና በየነ እና የእንጀራ አባቷ ብሩክ በሞት እንዲቀጡ ተወስኗል::
