የኢትዮጵያ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት (FDI) እና የውጭ ንግድ አፈጻጸም ከታቀደው በታች መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እንዳብራሩት፣ ለዚህም ዋነኞቹ ምክንያቶች ያልተተገበሩ እቅዶች እና የገበያ ለውጦች ናቸው ብለዋል።
ኮሚሽነር ዘለቀ እንደገለጹት፣ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ከእቅድ በታች የሆነበት ምክንያት፣ እቅዱ ሲዘጋጅ ታሳቢ ተደርገው የነበሩ እንደ የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ያሉ ጉዳዮች ባለመሳካታቸው ነዉ ሲል ተናግረዋል።
የውጭ ንግድ ከታቀደው በታች እንዲሆን ያደረጉትን ምክንያቶች ሲያብራሩ፣ ኮሚሽነሩ የሀዋሳ ልዩ ኢንዱስትሪ ዞንን እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል። በፓርኩ ውስጥ ለሚመረቱ አብዛኞቹ ምርቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበረው ፒቪኤች (PVH) የተባለው የአሜሪካ የልብስ ኩባንያ በነሐሴ ወር ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆሙ አንዱ ምክንያት ነው።
CapitalNews
