ዘመን ባንክ «ዚ ቀመር» የተሰኘ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አስጀመረ

Date:

ዘመን ባንክ «ዚ ቀመር» የተሰኘ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በዛሬው እለት አስጀምሯል:: ይህ አገልግሎት አዲስ የባንክ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን፤ የዘመን ባንክ የ17 ዓመት የልህቀት ጉዞ ቀጣይ ምዕራፍ ነው።

በመርሀግብሩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በዓለም ዙሪያ በፍጥነት እያደገ የመጣ ዘርፍ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፣ ዛሬ በትሪሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር የፋይናንስ ሀብትን የሚያንቀሳቅስ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ነው ተብሏል።

የዘመን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ደረጀ ዘበነ እንደገለጹት ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት የእምነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ልማት፣ የፋይናንስ አካታችነትና የዘላቂ ዕድገት መሣሪያ መሆኑንና በኢትዮጵያም የፋይናንስ አካታችነትን ለማስፋፋት፣ ያልተጠቀምንባቸውን አቅሞች ወደ መደበኛው የፋይናንስ ሥርዓት ለማምጣትና ከእምነት መርሆዎቻቸውና እሴቶቻቸው ጋር በሚጣጣም መልኩ የባንክ አገልግሎት ለሚፈልጉ ዜጎች አስተማማኝ አማራጭ ለመስጠት ይህ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

ወ/ሮ እንዬ ቢምር የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት “ይህ ምርት ለባንካችን አዳዲስ የገበያ እድሎችን የሚከፍት፣ የደንበኛ መሠረታችንን የሚያሰፋ፣ የተቀማጭ ሀብታችንን የሚያጠናክርና በሀገራችን በፍጥነት እያደገ ባለው ከወለድ ነፃ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ጠንካራ ቦታ እንድንይዝ የሚያስችል ነው::” በማለት ያለውን ጠቀሜታ አስገንዝበዋል፡፡

«ዚ ቀመር» የሚለው የአገልግሎት ስያሜ የ«ዘመን ባንክ»ን እና የ«ጨረቃ»ን ምልክት አንድ ላይ አጣምሮ እንደያዘ የተገለፀ ሲሆን «ዚ» (Zi) የሚለው የሚወክለው ዘመን ባንክን ሲሆን፣ «ቀመር» ደግሞ በአረብኛ ቋንቋ ጨረቃ ማለት እንደሆነ ተጠቁሟል ።

ዘመን ባንክ የሸሪዓ መርሆዎችን መሠረት ያደረጉ የ«ዚ ቀመር» ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶችን ተለይተው በተዘጋጁ መስኮቶችና ሙሉ በሙሉ ለዚህ ተብለው በሚከፈቱ ቅርንጫፎች አማካኝነት አገልግሎቱን እንደሚሰጥም ተነግሯል።

በዚህ «ዚ ቀመር» አማካኝነት ደንበኞች በሸሪዓ መርሆዎች የተቃኙ የቁጠባ፣ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ ፋይናንስና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በጥራትና በደንበኛ ተኮር አቀራረብ እንዲያገኙ አስፈላጊው ሁሉ ሲከናወን የቆየ ሲሆን፣ በቀጣይም የሚያስፈልጉት ነገሮች በሂደት ይከናወናሉ ተብሏል።

«ዚ ቀመር» ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን ለመጀመር ስልታዊ አቅጣጫ በመቀየስ ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱ ተነግሯል።

ዘመን ባንክ ከምስረታው ጀምሮ ለተወሰኑ ዓመታት በውስን ቅርንጫፎች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በ142 ቅርንጫፎች ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች

አንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ...

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው

ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል...

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን...

(IMF) ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

አዳዲስ ብድር በመውሰድ ረገድ ጥንቃቄ እንድታደርግ ኢትዮጵያን ያስጠነቀቀው IMF...