ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ቅዳሜ ይከበራል።
በዓሉን አስታኮ ግን አንዳንድ አገልግሎት ሰጪዎች ከፍ ያለ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ እንደሆነ በግልጽ ታይተዋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያም ” ጥቂት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዓሉን አስታከው በአንዳንድ አገልግሎቶችና በማረፊያ ቦታዎች ላይ ከወትሮው ውጭ የዋጋ ጭማሬ የሚመስሉ አዝማሚያዎችን እያደረጉ ስለመገኘታቸው ጥቆማዎች ቀርበውልኛል ” ብሏል።
” የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በእነዚህ አብዛኛው አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማይወክሉ ላይ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ቀደም ብለው እንዲታረሙ በጥብቅ ያሳስባል ” ሲል ገልጿል።
” ይህ አይነቱ ድርጊት በተለይም ሁላችንም የአይን ብሌን አድርገን የምናያትን ከተማችን የሀዋሳን ስም የሚያጠለሽ ሆኖ እንዳይገኝ ከወዲሁ በመሰል ድርጊት ላይ የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማስገንዘብ እንወዳለን ” ሲል መምሪያው አሳስቧል።
” በጥቆማው መሰረት በተጨባጭ መልኩ በዓሉን አስታከው ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ በማንኛውም አገልግሎት ላይ በሚያደርጉ አካላት ላይ አስተዳደሩ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል ” ብሏል።
@tikvahethiopia
