ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የአዲግራት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር የማነ ገብረማርያም ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል።
ፖሊስ በዶ/ር የማነ ላይ “ከፌደራል መንግሥቱና ከሐራ መሬት ታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላቸው” እንዲሁም “ወደ ሐራ መሬት ታጣቂዎች ሰዎችን እየመለመሉ ይልካሉ” የሚል ከባድ ክስ ማቅረቡን ጠበቃቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።
ይህንኑ ተከትሎ ፖሊስ ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ምክር ቤት ባወጣው አዋጅ መሠረት፤ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራውን ለማጠናቀቅ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ (የቀጠሮ ቀናት) ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፣ ጉዳዩ በክልሉ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል።
@Addis_New
