እኛን ለማጥፋት የሚፈልግን ኃይል አሸንፈናል፤ እናም አሁን ከጦርነቱ በኋላ እንደገና ሀገራችንን የመገንባት ስራ ጀምረናል ሲሉ ቤንያሚን ኔታንያሁ ገለጹ።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እኛን ለማጥፋት በፈለገችው የክፋት ዘንግ ላይ ትልቅ ስኬት እና ታላቅ ድል አድርጋለች ሲሉ በቅርቡ ከኢራን ጋር የገጠማትን ግጭት አስመልክተው በመግለጫቸው ተናግረዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
ኔታንያሁ ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ እስራኤል ከጦርነቱ በኋላ ያለውን የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ መጀመሯን አረጋግጣለሁ ብለዋል።
የእስራኤል ጦር የበላይነቱን በማሳየቱ የህልውና ስጋቶችን አስወግዷል ሲሉም ገልጸዋል።
ኔታንያሁ አክለውም “ሊያጠፉን ከሚፈልጉ ኃይሎች ጋር ጦርነት ገጥመን ከዛም የበለጠ ተጠናክረን ተባብረን ተወጥተነዋል” ብለዋል።
በሚቀጥለው ምዕራፍ እስራኤል ከመልሶ ግንባታ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች ከፊቷ በማስወገድ ሀገራችንን መገንባት አለብን ሲሉ ለህዝባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
