የምግብ ዘይት ፋብሪካዎች በፋይናንስ እና ግብዓት እጥረት 50 በመቶ ብቻ እየተጠቀሙ ነዉ

Date:

በኢትዮጵያ የሚገኙ የምግብ ዘይት አምራች ፋብሪካዎች በፋይናንስ እና በግብዓት እጥረት ምክንያት ከማምረት አቅማቸው 50 በመቶውን ብቻ እየተጠቀሙ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብ ዘይት አምራቾች ማኅበር አስታውቋል።

ማኅበሩ  እንደገለጸው፤ ዘርፉ ከፍተኛ ፋይናንስ የሚጠይቅ ቢሆንም በቂ በጀት እና የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ባለመኖሩ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት አልቻሉም።

የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ትልቅሰው ለታ፣ ፋብሪካዎቹ በሙሉ አቅማቸው አለማምረታቸው የምርት እጥረት እንዲከሰት ፣ የዋጋ ጭማሪ እንዲኖር እና የገበያ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ማድረጉን ገልጸዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው፣ የዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ካለፉት ዓመታት መሻሻል ቢያሳዩም አሁን ካለው የገበያ ፍላጎት አንጻር አቅርቦቱ ገና አለመመጣጠኑን አረጋግጠዋል።

ችግሩን ለመፍታት እና አምራቾች እንዲበረታቱ የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በተለይም የፋብሪካዎች የማምረት አቅም እንዲጎለብትና ተመጣጣኝ የገበያ አቅርቦት እንዲኖር ትኩረት መሰጠቱን አብራርተዋል።

የሀገር ውስጥ ዘይት አምራቾችን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር መንግሥት ከአበዳሪ ተቋማት ጋር በመሆን በቂ ብድር እንዲመቻች እና ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ምቹ ሁኔታ መፈጠር እንደሚገባው ተመላክቷል።

(አሐዱ ራድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...