የሬጌ ሙዚቃ ፈር ቀዳጁ ጂሚ ክሊፍ ህይወቱ አለፈ

Date:

ጃማይካዊው ጂሚ የሬጌ ሙዚቃን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ አድርጓል።

በተለይ ደግሞ በአውሮፓውያኑ 1970 እና 1972 የተጫወታቸው “You can get it if you really want” እና “The harder they come” ሙዚቃዎች ለድምፃዊው የግል እውቅና ብቻ ሳይሆን ሬጌ እንደ ሙዚቃ ዘውግ ለዓለም ያስተዋወቀባቸው ናቸው።

1962 ላይ ወደ ሙዚቃው ዓለም የተቀላቀለው ጂሚ ክሊፍ ከ30 በላይ የስቱዲዮ አልበሞችን ለአድማጭ ጆሮ አድርሷል::

በ1986 “Cliff Hanger” እና በ2013 “Rebirth ” አልበሞቹ የግራሚ ሽልማትን (Grammy Awards) በሬጌ ዘርፍ እንዲያሸንፍ አድርገውታል።

ባለቤቱ ላቲፋ ቻምበርስ በኢንስታግራም ባስተላለፈችው መልዕክት ባለቤቷ በሳምባ ምች ህመም ምክንያት በ81 ዓመቱ ህይወቱ ማለፉን አስታውቃለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...