የቤቲንግ ድርጅቶች ፈቃድ ተገደ

Date:

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የ22 የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የስፖርት ውርርድ ፈቃድ (ቤቲንግ ድርጅቶች) ከህዳር 25 ቀን 2018 ጀምሮ የታገደ መሆኑን አስታውቋል።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣  የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣  የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ አካላት እንዲሁም በኅብረተሰቡ ትብብር አማካኝነት ለመንግሥት ገቢ መሆን የነበረበትን ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰወር ወንጀል የተጠረጠሩ የስፖርት አወራራጅ ድርጅት ባለቤቶችና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው በይፋ መገለጹ ይታወቃል።

ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በተላከው መረጃ መሰረት ከዚህ በታች ስማቸው በዝርዝር የተጠቀሰው የስፖርት ውድድርና ውርርድ ድርጅቶች የወንጀል ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስ የስፖርት ውድድር ውርርድ የስራ ፈቃዳቸው ከዛሬ ጀምሮ ታግዷል፡፡

ፈቃዳቸው የታገደ የስፖርት  ውድድርና  ውርርድ ቤቶች ፦

  • ዳሽ ቤት ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • ዋልያ ስፖርት ኃ/የ/የግ/ማህበር
  • ኤክስኔት ሶሎሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር/ቱ ኤክስ ቤት/ 
  • ኤች ዲ ኤም /አፍሮ/ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • ብላክ ፐርል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • አይከኒክ ስፖርት ኢንተርቴይመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • ጃምቦ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማህበር 
  • ዳአባአክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • ኢቲኤል (ኪዉክ) ኃ/የ/የግ/ማህበር 
  • ቤትአራዳስፖርትእናኢንተርቴመንትኃ/የተ/የግ/ማህበር/ሱፐር/
  • ቫሞስ ኢንተርቴይመንት ኃ/የ/የግ/ማህበር – ፍላሽ ስፖርት ውርርድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • ሁለገብ ኦንላይን ሶሎሽን ኃ/የ/የግ/ማህበር
  • ዘመን ስፖርት ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • ሁሉ ጌሚንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር 
  • አዲስ ቴልኮ ሰርቢስ አክሲዮን ማህበር/ቤቲካ ስፖርት ውርረድ/
  • ዩኒክ /መላ/ስፖርት ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር 
  • ቶቶ ስፖርት ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • ኩኩሉ ስፖርት ስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • መርኬ ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር/ሻምፒዮን/
  • ቤት ዘጠኝ ዘጠና አራት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
  • ሀሪፍ የስፖርት አገ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...