የቤት ሠራተኞችን የሚመለከት ሞዴል ሕግ ማዘጋጀቱን ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ አስታወቀ

Date:

በግለሰብ ቤት ተቀጥረው የሚያገለግሉ የቤት ሠራተኞች ላይ ጥበቃና ደህንነት የሚሰጥ ሞዴል ሕግ ማዘጋጀቱን ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ የተሰኘ ሀገር በቀል የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅት አስታውቋል።

ይህንን ሞዴል ሕግ በመንግሥት በግብዓትነት መውሰድ እንደሚችል ተገልጿል።

የቤት ሠራተኞችን ብቻ የሚመለከት ራሱን የቻለ ሕግ መውጣቱ የሚፈፀሙ ጥቃቶችንና የመብት ጥሰቶችን ለማስቀረት እንደሚያግዝ የገለጹት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ ዶ/ር ሰላም ኢሳያስ ናቸው።

ዶ/ር ሰላም አዋጁ ተግባር ላይ እንዲውል የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ በሚወጣበት ወቅት፤ በተቻለ መጠን የቤት ሠራተኞችን ሃሳብ ማካተት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞችን የሚመለከት የተደራጀ ሕግ አለመውጣቱንና በፍትሃብሔር ብቻ የተቀመጠ ሕግ ስለመኖሩ የገለፁት ደግሞ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ሕግ ረዳት ፕሮፌሰር እና ተመራማሪ ሙሴ መዝገቡ ናቸው።

ረዳት ፕሮፌሰር ሙሴ እንዳሉት አዲሱ ሞዴል ሕግ የሠራተኞችን መብት እና ተጠቃሚነት የሚያስከብር፤ የአሰሪዎችን መብትም ታሳቢ ያደረገ ነው።

በመሆኑም “የኢትዮጵያ ቤት ሠራተኞች ጥበቃና ደህንነት” በሚል ስያሜ የተዘጋጀው ሕግ፤ የቤት ውስጥ ሠራተኞች በሳምንት የሚሰሩበትን ሰዓትና ከሥራ ሰዓት በላይ ከሰሩ ማግኘት ስለሚገባቸው መብት ይገልጻል።

ከዚህ በተጨማሪም ለሌሎች የመንግሥትና የግል ሠራተኞች ተፈፃሚ የሚሆነው የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል የቤት ሠራተኞችንም እንዲመለከት እንደሚጠይቅ አሐዱ ሰምቷል።

የክፍያ ሁኔታ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ሆኖ በጥሬ ገንዘብ እንደሚፈጸም እንዲሁም፤ የዓመት እረፍትና የሕመም ጊዜን ጨምሮ የመደራጀት መብትን የሚያስጠብቅ እንደሆነ ተነግሯል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...