የትራንስፖርት ክልከላዉ ተነስቷል

Date:



‎በጂንካ በተከሰተዉ የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ተጥሎ የነበረዉ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ክልከላ መነሳቱን የአሪ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ደምበላሽ አቦነሀሰ  ተናግረዋል።

‎ለክልከላዉ መነሳት ምክንያት የሆነዉ አሁናዊዉ የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት መቀነስና በትራንስፖርት መቋረጥ ምክንያት ማህበረሰቡ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መምጣቱን የዞኑ ግብረሃይል ከገመገመ በኋላ መሆኑን ገልፀዋል።

‎በመሆኑ ከቀን 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ክልከላው እንዲነሳ መወሰኑን  የገለፁት ኃላፊዉ ጉዞዎች ግን ከወትሮዉ በተለየ በጥንቃቄ መሆን እንዳለባቸውና በየመናኻሪያ የሚደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫና የጥንቃቄ ሂደቶች ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

‎ሕብረተሰቡና የተሽከርካሪ ባለንብረቶችም ይህንኑ በመረዳት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አቶ ደምበላሽ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...