በዓመት አንድ ጊዜ ሠራተኞቻቸውን የጉብኝት መዳረሻዎችን እንዲያስጎበኙ የሚያደርግ ደንብ ሊጸድቅ ነው

Date:

የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እድገትን ለማሳደግ በማሰብ ተቋማት ሠራተኞቻቸው በከተማዋ የሚገኙ የጉብኝት መዳረሻዎችን በዓመት አንድ ጊዜ እንዲያስጎበኙ የሚያደርግ ደንብ ወጥቶ እንዲጸድቅ ወደ የሚመለከተው አካል መላኩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን አስታውቋል።

በተለያዩ ተቋማት ወደ 74 የሚደርሱ የ”ሀገርን እንወቅ” ክበባት እንዲቋቋሙ መደረጉንና ነዋሪዎችም ጉብኝትን ባሕል ማድረግ እንዳለባቸው ለአሐዱ የተናገሩት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ ናቸው።

ኮሚሽነሩ ሁሉም ተቋማት በዓመት አንድ ጊዜ ሠራተኞቻቸውን መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ የሚያስችል፤ በሕግ የተደገፈ ደንብ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ማበረታቻ የሚባል ደንብ መውጣቱንና እንዲጸድቅ ወደ የሚመለከተው አካል መላኩን አስታውሰዋል። ሀገርን እንወቅ ክበባትን በከተማዋ በሚገኙ በመንግሥትና በግል ተቋማት ጭምር እንዲስፋፉ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

የውጭ ጎብኚዎችን ከማሳደግ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን የማበረታታት ሥራ እየተሰራ መሆኑን የገለጹም ሲሆን፤ ዘርፉ ለሀገር ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ያለው ሚና ትልቅ እንደሆነ ተናግረዋል። 

የሚጎበኙ ስፍራዎች እንዳሉ ሆነው፤ ኮሚሽኑ የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ሀገራት በፍጥነት እያደገ የመጣውን የቱሪዝም ወይም ጭስ አልባው ኢንዱስትሪን በማጎልበት የሀገራቸውን ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ መስህቦችን በማልማትና ለሀገርና ለዓለም በማስተዋወቅ እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ ናት።

እነዚህን ሀብቶች በይበልጥ በጥናት በመለየትና በመጠበቅ ለትውልድ እንዲተላላፍ በማድረግ ጠንካራ የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ሀብቶችን ለዓለም ማህበረተሰብ በማስተዋወቅ ለወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል በማስፋት፤ ቱሪዝም በብሔራዊ ኢኮኖሚ ውስጥ በተገቢው ድርሻ እንዲያበረክት ውጥኖችን ማሳካት እንደሚጠበቅባት የዘርፉ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወቃል።

አሐዱ ሬዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...