የአሜሪካው አምባሳደር ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ገቡ

Date:

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ከተማ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ረፋዱን ገብተዋል። አምባሳደሩ ሁመራ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለውና ሌሎች ከፍተኛ የዞኑ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አምባሳደር ማሲንጋ ወደ አካባቢው ያቀኑት በዞኑ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ከአመራሮቹ ጋር ለመወያየትና በስፍራው የሚገኙ የጤና ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ለመመልከት መሆኑ ታውቋል።

አምባሳደሩ በቆይታቸው በሰቲት ሁመራ የሚገኙ የጤና ተቋማትን የመሰረተ ልማትና የግብዓት አቅርቦት ሁኔታ በአካል ተገኝተው እንደሚጎበኙ ይጠበቃል። በተጨማሪም ከዞኑ አመራሮች ጋር በሚያደርጉት ውይይት፣ በአካባቢው ሰብአዊ ድጋፎችን ማጠናከር በሚቻልበትና ተያያዥ የልማት ስራዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ይህ ጉብኝት በስትራቴጂካዊቷ የድንበር ከተማ ሁመራ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለመረዳት እንዲሁም የአሜሪካ መንግስት በጤናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...