ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና፣ የ7.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግበትን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ በዋናነት እንዲያስተባብር የሚያስችለውን ስምምነት ሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአቡሴራ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ በየዓመቱ 60 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል።
ይህ አቅም ሙሉ በሙሉ ሲጠቀም እስከ 110 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን ማስተናገድ ይችላል። የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ የግንባታ ምዕራፍ እ.ኤ.አ. በ2025 መጨረሻ ላይ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
CapitalNews
