የኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋት መጥፊያዋ እንደሚሆን ገለጹ

Date:

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ሃገራቸው አሜሪካ ወደ ጦርነት ውስጥ የገባችው ከኢራን ጋር ሳይሆን ከኒውኪሊየር ፕሮግራሟ ጋር እንደሆነ ተናግረዋል።

በ100% መተማመን የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የኒውኪሊየር ጣቢያዎች አጥፍቷል ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “ወደ እንደዚህ አይነት የደህንነት መረጃዎች መግባት አልፈልግም፤  የአሜሪካ የምሽቱ ጥቃት ግን የኢራንን ኒውኪሊየር የመታጠቅ አቅም በእጅጉ አዘግይቶታል” ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምሽቱ ጥቃት የኢራን የኒውኪሊየር ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን ሲገልፁ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ብቻ መግለፃቸው ይታወሳል።

ኢራን አሜሪካን ካጠቃች ከባድ ኃይል እንደሚጠብቃት የተናገሩት ም/ፕረዚዳንቱ “ እኛ ንፁሃንን ኢላማ አላደረግንም፤ ከሶስቱ የኒውኪሊየር ጣቢያዎች ውጪ እንኳን ባለ ወታደራዊ ቦታ ላይ ጥቃት አልፈፀምንም” ብለዋል።

ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ያለውን የመርከብ እንቅስቃሴ ልትረብሽ ትችላለች በሚል የተጠየቁት ጄዲ ቫንስ “እሱ ለኢራን መጥፊያዋ ይሆናል” ሲሉ መልሰዋል።

ቫንስ “ ኢራናውያን በጦርነት ጥሩ አይደሉም፤ በፕሬዚዳንቱ የተሰጣቸውን የሰላም ዕድል ሊጠቀሙ ይገባል “ ብለዋል።

SOURCE: NBC NEWS

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...