የኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይል

Date:

የኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ “ፊዚካል ጥናት” መጀመሩን የአይሲቲ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዲኤታው አስታወቁ

“መንግስት የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ልማት ላይ ከሩሲያ መንግስት ጋር አብሮ በመስራት ላይ ይገኛል ” ሲሉ ይሽሩን አለማየሁ ተናገሩ።

ሩሲያ በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን እገዛ አስመልክቶ ነፃ የትምህርት እድሎችን እንደማሳያ የጠቆሙት ሚኒስትር ዲኤታው ፤ በአዲስ አበባ ከተካሄደው የኢኖቬሽን አፍሪካ 2025 የትምህርት፣ የአይሲቲ እና የክህሎት ሚኒስትሮች ጉባዔ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

“ሩሲያ የምታደርግልንን እገዛ እናደንቃለን፤ ድጋፏንም እንድትቀጥል እንፈልጋለን” ብለዋል።

ይሽሩን አክለውም ሩሲያ እያደረገች ያለችው ሀገር በቀል እውቀቶችን እና አቅምን ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ማሳየት ነው ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ውጭ ምንዛሪ የሚያድኑ የሴራሚክ ምርቶች በቅርቡ ለገበያ ይቀርባሉ

ይህ የተገለፀው ኢትዮደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ”Golden Tier...

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...