የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት በሚያዚያ ወር 14.4 በመቶ ደርሶ እንደተመዘገበ የኢትዮጵያ የስታትስቲክስ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ አሃዝ ከመጋቢት ወር 13.6 በመቶ የዋጋ ግሽበት ጋር ሲነጻጸር የ0.8 በመቶ ጭማሪ ያሳያል።
በሚያዚያ ወር ከተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ውስጥ ምግብ ነክ ዕቃዎች 12.2 በመቶ ድርሻ ሲይዙ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ 17.9 በመቶ ደርሷል። ይህ የሚያሳየው ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ዋጋ መጨመር በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።
CapitalNews
