የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ 84 አዳዲስ ብሔራዊ ደረጃዎችን አጸደቀ

Date:

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ በቅርቡ ባካሄደው 3ኛ መደበኛ ስብሰባው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ እና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ 84 አዳዲስ ብሔራዊ ደረጃዎችን መርምሮ አጽድቋል።

እነዚህ ደረጃዎች 68 አስገዳጅ መመሪያዎችን እና 16 የፍተሻ ዘዴዎችን ያካተቱ ሲሆን፣ በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ተከፋፍለው ወደ ተግባር እንዲገቡ ተወስኗል።

በኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች ዘርፍ በተፈጥሮ ጋዝ ምርቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ 9 አስገዳጅ ደረጃዎች እና 11 የፍተሻ መመሪያዎች ሲጸድቁ፣ በኤሌክትሮ ሜካኒካል ዘርፍ ደግሞ የተፈጥሮ ጋዝ መሰረተ ልማትን፣ የኃይል ፋክተር ማስተካከያን እና የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን (በተለይም ፍሪጅን) የሚመለከቱ 36 አዳዲስ ደረጃዎችና የፍተሻ ዘዴዎች ተካተዋል።

በተጨማሪም በኮንስትራክሽን እና ሲቪል ምህንድስና ዘርፍ የብረትና አልሙኒየም መዋቅሮችን ጥራት የሚቆጣጠሩ 28 አስገዳጅ ደረጃዎች መጽደቃቸው ታውቋል።

እነዚህ ደረጃዎች የወቅቱን የሀገሪቱን ፖሊሲ መሰረት በማድረግ የተዘጋጁ ሲሆኑ፣ በተለይም ኢትዮጵያ በቅርቡ ወደ ገበያ ለምታስገባው የተፈጥሮ ጋዝ ምርት የጥራት ቁጥጥርና ደህንነቱ የተጠበቀ ስርጭት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...