የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አከባቢ ለሚያስገነባዉ ባለ 62 ፎቅ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታ ዓለም አቀፍ የቅድመ-ማጣሪያ ጨረታ ማዉጣቱን አስታዉቋል ።
ይህ ግዙፍ ሕንፃ በ445 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚገመት ኢንቨስትመንት የሚካሄድበት ሲሆን፣ ኢኢኃ በንግድ ግንባታ ዘርፍ ልዩ ሙያ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ተቋራጭ ድርጅቶች ለጨረታው እንዲወዳደሩ ጋብዟል።
በአዲስ አበባው የፋይናንስ ማዕከል በ20,792 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚገነባው ይህ ሕንፃ በኢንጂነሪንግ፣ ግዥ እና ኮንስትራክሽን (EPC) የውል ዓይነት የሚከናወን ሲሆን፣ ሲጠናቀቅም 197,800 ካሬ ሜትር የሆነ አጠቃላይ የወለል ስፋት እና 327.5 ሜትር ከፍታ እንደሚኖረውና በ 4 ዓመታት ዉስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዟል።
CapitalNews
