የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ ክርስቲያኖ ጁኒየር የመጀመሪያ ዋንጫውን አነሳ

Date:

ለመጀመርያ ጊዜ ለፖርቹጋል  ከ15 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገለት ክርስቲያኖ ጁኒየር የቭላትኮ ማርኮቪች ዋንጫን አሳክቷል።

በቀድሞው የክሮኤሽያ አንጋፋ ተጫዋች አሰልጣኝ እና የፌደሬሽኑ ፕሬዝደንት ቭላትኮ ማርኮቪች ስም በተሰየመው ወድድድር ፖርቹጋል ክሮኤሽያን 3 ለ 2 ባሸነፈችበት ጨዋታ ሁለት ግቦችንም አስቆጥሯል።

ልክ እንደ አባቱ 7 ቁጥር መለያ ለብሶ ሚጫወተው ጁኒየር ለሰባተኛ ጊዜ በተደረገው የመታሰቢያ መድረክ  ባሳየው ብቃት ብዙዎችን አስደንቋል።

በተለይም የመጀመርያ ግቡን ካስቆጠረ በኋላ  እንደ አባቱ ክርስቲያኖ ሁሉ ደስታውን በተመሳሳይ መንገድ ገጿል።

በልጁ እንቅስቃሴ ደስተኛ መሆኑን የተናገረው የአል ናስሩ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ምንም እንኳን በመካከላቸው የ26 አመት ልዩነት ቢኖርም በአንድ ወቅት ከልጁ ጋር መጫዎት እንደሚፈልግ መናገሩም ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...