የዓለም ጤና ድርጅት በኢራን የጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን ገለጸ

Date:

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፣ በኢራንና በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ ባለው ግጭት ሳቢያ በዋና ከተማዋ ቴህራን በሚገኙ የጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ገልጸዋል።

ከእነዚህም መካከል ከ1920 ጀምሮ ለአንድ ክፍለ ዘመን በምርምርና በህክምና ሲያገለግል የቆየው ታዋቂው የፓስተር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት አገልግሎት ማቋረጡን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የደላራም ሲና የአእምሮ ህክምና ሆስፒታልና ለካንሰርና 1111111q@qqqql00000¡@ለሌሎች በሽታዎች መድኃኒት የሚያመርተው የቶፊቅ ዳሩ ፋብሪካ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን በዝርዝር አስፍረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ከመጋቢት ወር መጀመሪያ አንስቶ በኢራን የጤና ተቋማት ላይ ከ20 በላይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ድርጅታቸው ማረጋገጡንና በዚህም የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጸዋል።

ጥቃቶቹ ከቴህራን ውጪም በመስፋፋት በኢማም አሊ ሆስፒታል ላይ በደረሰ ፍንዳታ ህመምተኞች እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። ግጭቱ የጤና ባለሙያዎችንና የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ መሆኑን ያሳሰቡት ዋና ዳይሬክተሩ፣ “ሰላም ከሁሉ በላይ መድኃኒት ነው” በሚል ጥሪ መልዕክታቸውን ደምድመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የታላቁ ምሁር መታሰቢያ በድምቀት ተካሄደ

የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ሁለተኛ ዓመት...

የኩላሊት እጥበት ማዕከል ለማቋቋም የሚያስችል ጥናት ተዘጋጀ

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የኩላሊት ህመም ስርጭት...

ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረውን የ‘ሴሬብራል ፓልሲ’ ቀን የእግር ጉዞ ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የ‘ሴሬብራል ፓልሲ’ ቀንን...

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...