በ”ፊንቴክ” ኢንቨስትመንት በተጠረጠሩት ላይ ተጨማሪ ጊዜ ተፈቀደለት

Date:

ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን ለምርመራ እንዲፈቀድለት ባለፈው አርብ በነበረው ችሎት  ጠይቆ ለውሳኔ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ቀጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በ”ፊንቴክ”(Fintech) ኢንቨስትመንት ሽፋን በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮችን ጉዳይ ፖሊስ በጠየቀው የተጨማሪ ጊዜ ላይ ለመወሰን የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ለፖሊስ የ7 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

ባለፈው ሚያዚያ 9 2018 ዓ/ም በነበረው ችሎት ባለፉት ቀናት  ያከናወናቸውን ተግባራት ለችሎቱ ያስረዳው ፖሊስ፣ ነገር ግን ከወንጀሉ ውስብስብነትና ስፋት አንፃር ቀሪ የምርመራ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር። 

በተቃራኒው የተጠርጣሪዎች ጠበቆች ደንበኞቻቸው በህዝብ ዘንድ የሚታወቁና ቋሚ መኖሪያ ያላቸው መሆኑን እና የራሳቸው መተዳደሪያ ስራ ያላቸውና አብዛኞቹም የጤና እክል ያለባቸው ናቸዉ በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ተከራክረዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ሚያዚያ 14 2018 ዓ/ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

ዛሬ በነበረው ችሎት ፖሊስ የቀረውን ምርመራ አጠናቆ እንዲያቀርብ 7  ተጨማሪ ቀናት ፈቅዷል።

ተጠርጣሪዎቹ ለቀጣይ የችሎት ቀጠሮ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዟል።

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...