የጤና ሚኒስቴር ከልማት አጋሮች ጋር በዘርፉ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶች ላይ ተወያየ

Date:

የጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድን (HSDIP II) ግቦች ለማሳካትና ትብብርን ለማጠናከር ከልማት አጋሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር ፍሬያማ ውይይት አካሄደ።

በወቅቱ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የሀገራዊ የጤና ዘርፉን ወቅታዊ ሁኔታ ለአጋሮች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ በተለይም በዓለም አቀፍ ክስተቶች ሳቢያ ሊያጋጥሙ የሚችሉ መስተጓጎሎችን ለመቋቋም የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንና ትኩረት የሚሹ አበይት የጤና ጉዳዮችን አስረድተዋል።

በቀጣይ ዓመታት የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ለመምራት የተነደፈው HSDIP II ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ፍትሃዊ ተደራሽነትን በማስፋፋት፣ የጤና ስርዓቱን የመቋቋም አቅም በማጠናከርና ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ጉዞን በማፋጠን ላይ ያተኮረ እንደሆነ ሚኒስትሯ በዝርዝር አብራርተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ሀብት ማሰባሰብን ማሻሻልና በጤና ስርዓቱ ውስጥ ቅልጥፍናን ማረጋገጥ የዕቅዱ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ግቦች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ስብሰባውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና አጋሮች ኢንቨስትመንት ዕቅዱን በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት በማጠናከር ተጠናቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...