የሰባት ዓመቱ የኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤቶች

Date:

ባለፉት ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ
የፊስካል ፖሊሲና የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ላይ ጉልህ ስኬቶች መመዝገባቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከ2010 እስከ 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች የመንግስት የበጀት ጉድለትን ከሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት የነበረበትን -2.5 በመቶ ወደ -0.9 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል።

በገቢ አሰባሰብ ረገድ የተወሰዱ የፖሊሲ እርምጃዎች ጠቅላላ የመንግስት ገቢን ከ5 እጥፍ በላይ ያሳደጉ ሲሆን፣ በተመሳሳይ መልኩ ድህነት ተኮር ወጪዎችም ከ5 እጥፍ በላይ እንዲያድጉ ተደርጓል።

የበጀት ተዓማኒነትን ለማረጋገጥ የመካከለኛ ዘመን የፊስካል ማዕቀፍ እንዲጠናከር መደረጉ ለአፈጻጸም መሻሻል ትልቅ ድርሻ አበርክቷል።

በተለይም የዋጋ ንረትን ለመግታት ከመንግስት ማዕከላዊ ባንክ የሚወሰደው ቀጥታ ብድር እንዲቀር መደረጉ በዋና ስኬትነት ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር የመረጃ ስርዓት (IFMIS) እና የዲጂታል ክፍያ አማራጮችን በመተግበር፣ የመንግስት የፋይናንስ ስርአቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን ረገድ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...