የጥርስ ህክምና ማስታወቂያዎች አብዛኛዎቹ ግነት ይታይባቸዋል

Date:

በዛሬዉ ዕለት የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የጥርስ ህክምና ማህበር ጋር በመሆን የጥርስ ህክምና አገልግሎት መስጫ ጤና ተቋማት ባለቤቶችና በጤና ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጤና ተቋማት የሚሰሩ ማስታወቂያዎች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ግምገማ አካሄዷል ።

በዉይይቱም በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፋ የጥርስ ህክምና ማስታወቂያዎችን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ማስታወቂያዎች ግነት የበዛባቸው መሆኑንና አንዳንዶቹም ከባህላችን የወጡ መልዕክቶችን ያዘሉ መሆናቸዉን በጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዮርዳኖስ አለባቸዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ሜሮን ያዕቆብ በበኩላቸው ከጥርስ ህክምና ጋር  የተያያዙ ወጣ ያሉ የማስታወቂያ ስራዎችን በተመለከተ የሚስተዋሉ ግነቶች መዘዝ ሳያመጡና ወደ ሌሎችም ሙያዎች ሳያዛመቱ እንዴት ወደ መስመር ማስገባትና መቆጣጠር ይቻላል የሚለዉ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል ።

በተለያዩ ማሕበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ግነት የበዛባቸዉ ከመሆናቸዉ ባሻገር ከማህበረሰባችን ባህልና ወግ የወጡ አንዳንዶቹም ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚይዙ በመሆናቸዉ ትኩረት በመስጠት የማስታወቂያ ኢንዱስትሪው ላይ እንዴት እንስራ የሚለዉ ላይ ሰፊ ዉይይት ተካሄዷል።
#ዳጉ_ጆርናል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...