“የሊቨርፑል ስኬት የልብ ህመም ነው”:- ኔቭል

Date:

ከቶተንሀም የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አድርገው ቶተንሀምን አሸንፈው ታሪክ የሰሩት አርን ስሎት

ቶተንሀም ሆትስፐርስ ከአንቶኒዮ ኮንቴ ጋር ከተለያየ በኋላ አርን ስሎትን ለመሾም ቢፈልግም አሰልጣኙ በፌይኖርድ መቆየትን ምርጫቸው አደረጉ።

ከአንድ አመት በኋላ ግን ስኬታማውን አሰልጣኝ የርገን ክሎፕን ተክተው አንፊልድ ደረሱ።

ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የሊቨርፑልን የ30 አመት የፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ርሀብ ማስታገሳቸው እና ብዙም እንግዳ በማይሆኑበት የአውሮፓ መድረክ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማሳካታቸው እንዲሁም ደብዝዞ የነበረውን የክለቡን የአልሸነፍ ባይነት ስሜት መልሰው ከቀዮቹ ጋር በክብር ሲለያዩ የሁሉም ጥያቄ የነበረው ማን ይተካቸዋል የሚለው ነበር።

የተመረጡት ሰው ደግሞ የቶተንሀምን ጥያቄ ውድቅ አድርገው በፌይኖርድ የቆዩት አርን ስሎት ቢሆኑም መገናኛ ብዙሀኑ እና ጸሃፊዎች የተቀበሏቸው በማስፈራራት ነበር።

ከፈረንጆቹ ገና በፊት ይሰናበታሉ፣ ሊቨርፑል ማንችስተር ዩናይትድ የሰራውን ስህተት ደገመ፣ በሊጉ ከተሰናባቾቹ የመጀመርያው ይሆናሉ፣ ወደ አለማችን አስፈሪው ሊግ እንኳን በደህና መጡ፣ ለቀጣይ ሁለት አመት ሊቨርፑል የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ማሰብ የለበትም፣ ዋናው አሰልጣኝ ማነው? የሚሉት እና ሌሎችም ስሜትን የሚፈታተኑ ሃሳቦች በእንግዳው ሰው ላይ የተሰነዘሩ ናቸው።

የ46 አመቱ አሰልጣኝ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ የተጠራጠሯቸውን ለማሳመን ጊዜ እንኳን አላባከኑም።

ከፌደሪኮ ኬዛ ውጭ ስም ያለው ተጫዋች ሳያስፈርሙ የጠንካራውን ጉዞ ሊግ የጀመሩት ሰው ሻምፒዮን እስኪሆኑ ድረስ የተሸነፉት በኖቲንግሀን ፎረስት እና በፉልሀም ብቻ ሲሆን በ34ኛ ሳምንት ቶተንሀምን አሸንፈው ከሊጉ ክብር ጋር ተገናኝተዋል።

ከክሎፕ የጨዋታ መንገድ የተወሰነ ለውጥ አድርገው በቀጥተኛ አጨዋወት ስኬታማ የሆኑት አሰልጣኙ ሙሀመድ ሳላ ሪያን፣ ግራቨን ብሪች እና ቨርጂል ቫንዳይክን ከ34 የሊግ ጨዋታ በ33ቱ ቋሚ አድርገው የተጠቀሟቸው ተጫዋቾች ናቸው።

ሊቨርፑል በ1990 በኬኒ ዳግሊሽ እየተመራ ኪው ፒ አርን አሸንፎ አንፊልድ ላይ ዋንጫ ማንሳቱን ካረጋገጠ ከ35 አመት በኋላ አርን ስሎት የቀዮቹን ደጋፊዎች በሜዳቸው ደስታቸውን አንዲጋሩ አድርገዋል።

በእርግጥ የርገን ክሎፕ የክለቡን 19ኛ ዋንጫ በ2020 ሲያነሱ ደጋፊዎች ዕድሉን ቢያገኙም ወቅቱ ኮቪድ ስለነበር በሚፈልጉት ልክ ተሰባስበው የተደሰቱበት አልነበረም።

ባስመዘገቡት ውጤት ተቺዎቻቸውን ዝም ያስባሉት ሰው ማንችስተር ዩናይትድ ለአመታት ብቻውን የያዘውን የ20 ጊዜ ሻምፒዮንነት ታሪክ በመጋራታቸው ብቻ በአንድ ጊዜ የእንግሊዝ ስኬታማው ክለብ የሀይል ሚዛን ከማንችስተር ከተማ ወደ መርሲሳይድ ተቀይሯል።

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ጋሪ ኔቭል “ክርክሩ አብቅቷል ምክንያቱም በሊጉ እኩል ብንሆንም በአውሮፓ መድረክ ሊቨርፑል ከእኛ የተሻለ ዋንጫ አለው የሊቨርፑል ስኬት ለእኛ የልብ ህመም ነው” ብሏል።

አርን ስሎት ከጆዜ ሞሪኒሆ፣ ካርሎ አንቾሎቲ፣ ማኑኤል ፔሌግሪኒ እና አንቶኒዮ ኮንቴ በመቀጥል በመጡበት አመት የሊጉን ዋንጫ ማሳካት የቻሉ 5ኛው አሰልጣኝ ሆነዋል።

በአንተነህ ሲሳይ ebc

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...