በኢትዮጵያና በፓኪስታን መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 133 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ተከትሎ፣ የፓኪስታን ንግዶች እንደ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣ ጨርቃጨርቅና የቆዳ ውጤቶች ያሉ የኢትዮጵያ ምርቶችን በስፋት እንዲጠቀሙባቸው ጥሪ ቀረበ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ደኤታ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ እንደተናገሩት፣ እ.ኤ.አ በ2024 ዓ.ም. ከተመዘገበው አጠቃላይ የ133 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ውስጥ፣ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ድርሻ 74.4 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ወደ ሀገር ዉስጥ ያስገባችው ድርሻ ደግሞ 58.6 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።
ሚኒስትር ደኤታው ይህንን የገለጹት ከፓኪስታን ንግድ ልማት ባለሥልጣንና በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የንግድ ክፍል ጋር በመተባበር 5ኛውን የፓኪስታንና የአፍሪካ የንግድ ልማት ጉባዔና የፓኪስታን ምርቶች ኤግዚቢሽን፣ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ ባስጀመረበት ወቅት ነው።
CapitalNews
