ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም አገደ

Date:

የለንደን ፍርድ ቤት ደቡብ ሱዳን ከአሁን በኋላ አዳዲስ የነዳጅ ኤክስፖርት ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም ወይም ለብድር መያዣነት የወደፊት የነዳጅ ጭነቶችን እንዳታስይዝ እገዳ መጣሉ ተዘገበ።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ቢቢ ኢነርጂ የተሰኘው የነዳጅ ንግድ ኩባንያ ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ሊሰበስበው የሚገባውን 100 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ ለማስመለስ የሚያደርገውን ሕጋዊ ትግል ተከትሎ ነው።

ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ትዕዛዝ አገሪቱ ከየትኛውም ሦስተኛ ወገን ጋር በ‘ዳር ብሌንድ’ ወይም ‘ናይል ብሌንድ’ ድፍድፍ ነዳጅ ሽያጭ ላይ የቅድመ-ክፍያ ስምምነት እንዳታደርግ የሚከለክል ሲሆን፣ ትዕዛዙን የሚጥሱ አካላት (ባንኮችም ሆኑ ሌሎች ነጋዴዎች) የፍርድ ቤት መናቅ ወንጀል ተቆጥሮባቸው ለእስራት፣ ለገንዘብ መቀጫ ወይም ለንብረት መወረስ ሊዳረጉ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

የነዳጅ ኤክስፖርት የደቡብ ሱዳን ዋና የገቢ ምንጭ ቢሆንም፣ በጦርነት የምትታመሰው አገሪቱ ባለፉት ዓመታት ከባንኮችና ከነጋዴዎች የወሰደችውን ብድር በነዳጅ ለማካካስ የገባችውን ቃል በተደጋጋሚ በማፍረስ ነዳጁን ለሌሎች ገዢዎች ስትሸጥ መቆየቷ ተገልጿል።

ቢቢ ኢነርጂ ባለፈው ዓመት ባገኘው ሌላ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አንድ የነዳጅ ጭነት መረከብ የቻለ ሲሆን፣ አዲሱ ጠንከር ያለ እገዳ ደግሞ የቀረውን ዕዳ ሙሉ በሙሉ ለማስመለስ እንደሚያግዘው አስታውቋል።

ደቡብ ሱዳን በዚህ የለንደን የፍርድ ቤት ክርክር ላይም ሆነ ቀደም ሲል ከአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ጋር በነበረባት የ657 ሚሊዮን ዶላር ክስ ላይ ተገኝታ ለመከራከር ሕጋዊ ወኪል ያላሰማራች ሲሆን፣ የአገሪቱ ገንዘብ ሚኒስቴርም በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 9 ወራት 83,000 ህፃናት ተወልደዋል

ከሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ዘግይተው...