በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው 4ኛው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ በመሳተፍ ታላቅ ድልና ውጤት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በደማቅ የጀግና አቀባበል
ተደርጎለታል ።
በውድድሩ የሀገራችንን ስምና ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው ያስጠሩት ጀግኖች አትሌቶቻችን፣ አሰልጣኞችና የልዑክ ቡድኑ አባላት በአየር ማረፊያው በተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል የድላቸውን ደስታ ከሕዝባቸው ጋር ተጋርተዋል።
እንኳን በሰላም ወደ ሀገራችሁ ተመለሳችሁ! በድላችሁም እንኮራለን!
