ጋና ለግብረሰዶማውያን የ3 ዓመት እስራት ደነገገች

Date:

​የጋና ፓርላማ የሀገሪቱን ባህላዊና ቤተሰባዊ እሴቶች ለመጠበቅ በሚል ግብረሰዶማዊነትን እና የኤል.ጂ.ቢ.ቲ.ኪው እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉ የሚያግድ ጥብቅ ህግ አጽድቋል።

በአዲሱ ድንጋጌ መሰረት፣ ራሳቸውን እንደ ግብረሰዶማዊ አድርገው በሚገልጹ ግለሰቦች ላይ እስከ 3 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ይፈረድባቸዋል።

​የህጉ አቅራቢ የሆኑት ሰበካው ጆን ንቲም ፎርድጆር፣ እርምጃው የጋናን ማህበረሰባዊ እሴት ለማስከበርና ፍትህን ይበልጥ ጠንካራ ለማድረግ የታለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ሕጉ ግብረሰዶማውያንን ከመቅጣት ባለፈ፣ ማንኛውም ዜጋ መሰል እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት ለፖሊስ የመጠቆም ህጋዊ ግዴታ ጥሎበታል።

ይህ የጋና እርምጃ በቅርቡ ተመሳሳይ ህጎችን ካጸደቁት እንደ ሴኔጋል እና ኡጋንዳ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ ጋር የሚቀራረብ ሆኗል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...