ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፈረንሳይ ገቡ

Date:

የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ የሁለትዮሽ ትብብር በብዙ ዘርፎች መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን  ጋር  ዛሬ ማምሻውን በፓሪስ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር  ግንኙነታችንን እና ትብብራችንን በሚያጠናክሩ ሰፋ ያለ መጠነ ርዕይ ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መወያየት ምንግዜም አስደሳች ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ለተደረገልን ደማቅ አቀባበል እና በታኅሳስ ወር በአዲስ አበባ ከነበረን ውይይት ቀጥለን ስላካሄድነው ፍሬያማ ውይይት ምስጋናዬን እገልጻለሁ ብለዋል።

ትብብራችን በብዙ ጠቃሚ ዘርፎች የቀጠለ ሲሆን የንግድ ትስስሮቻችንን የበለጠ ማሳደግ ከቅድሚያ የትኩረት ማዕከሎቻችን አንዱ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...