ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

Date:

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ በመክፈት ከፍተኛ ግርግር የፈጠረው ተጠርጣሪ ማንነት ይፋ ሆኗል። የ31 ዓመቱ የካሊፎርኒያ ቶራንስ ነዋሪ የሆነው ኮል ቶማስ አለን፣ ዓመታዊው የእራት ግብዣ በሚካሄድበት ዋሺንግተን ሂልተን ሆቴል አዳራሽ ውጭ ተኩስ የከፈተው ግለሰብ መሆኑን የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘግበዋል። ክስተቱን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በልዩ ጥበቃ በፍጥነት ከስፍራው ሲሸሹ፣ ታዳሚዎች፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ሰዎች መሬት ላይ ለመደፋት ተገደው ነበር።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ የተጠርጣሪውን ፎቶ እና ቪዲዮ በማጋራት፣ ጥቃት አድራሹን “በጠና የታመመ ሰው” እና “ወንበዴ ” ሲሉ ጠርተውታል።

የአሜሪካ አቃቤ ሕግ ጂኒን ፒሮ ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደገለጹት፣ በአለን ላይ የጦር መሣሪያ መጠቀምን እና በአደገኛ መሣሪያ የፖሊስ ኦፊሰርን ማጥቃትን ጨምሮ ሁለት ክሶች የተመሰረቱበት ሲሆን፣ ሌሎች ተጨማሪ ክሶችም በቅርቡ ሊከተሉ ይችላሉ። ከተኩሱ በኋላ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ባለሥልጣናት ተጠርጣሪው በሂልተን ሆቴል ክፍል ተከራይቶ አዳሪ እንደነበር እና “ሾትጋን (shotgun)፣ ሽጉጥ (handgun) እና በርካታ ቢላዋዎችን” ታጥቆ እንደነበር አረጋግጠዋል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ አለን እ.ኤ.አ. በ2017 ከካልቴክ ዩኒቨርሲቲ በሚካኒካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ደግሞ በኮምፒውተር ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪውን አጠናቋል።

በሊንክድኢን ገጹ ላይ ራሱን “በዲግሪ ሚካኒካል ኢንጂነር እና የኮምፒውተር ሳይንቲስት፣ በልምድ ራሱን የቻለ የጌም አበልጻጊ፣ እንዲሁም በተፈጥሮ ደግሞ መምህር” በማለት ይገልጻል። በአሁኑ ቀጣሪው “ሲቱ ኤጁኬሽን” ውስጥ “የወሩ ምርጥ መምህር” ተብሎ ተሸልሞ እንደነበርም በገጹ ላይ አስፍሯል።

እስካሁን ባለው መረጃ፣ አለን ይህንን ጥቃት ብቻውን እንዳቀደ እና እንደፈጸመ ይታመናል። በአሁኑ ወቅት ለፖሊስ ጥያቄዎች መልስ ከመስጠት የተቆጠበ ቢሆንም፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ኢላማ ማድረጉን የሚጠቁም ንግግር አድርጎ እንደነበር (ምንም እንኳን የተወሰነ ሰው ስም ባይጠቅስም) የምርመራ ባለሥልጣናት ለኤቢሲ ኒውስ አረጋግጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...