በመላው ኢትዮጵያ ያሉት የግል ህክምና ተቋማት ብዛት ከ28,000 በላይ ነዉ

Date:

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ይህንን ያሉት በ30 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት የተቋቋመውንና ኑቢራ በሚል መጠሪያ የተሰየመውን  የህክምና ማዕከል  መርቀው ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት የግል የጤና ተቋማት በቁጥር ከመንግስት የጤና ተቋማት ይበልጣሉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በቁጥር መብለጥ ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ የህክምና ክፍያ እንዲኖራቸው እንዲሁም የተሻለ ህክምና የሚሰጡ እንዲሆኑ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ኑቢራ የሕክምና ማዕከል የዘርፉኑ ስታንዳርድ (ደረጃ)  በሚጠይቀው መንገድ በርካታ የሥራ ክፍሎችን በተደራጀ መንገድ ወደ ሥራ መግባቱን ተመልክተናል፤


የጤና ሚኒስቴር የግል የጤና ተቋማት በሚያስፈልጋቸው ሁሉ በመደገፍ ወደ ውጭ የሚደረግን የህክምና ጉዞ ከማቀረት አልፎ አዲስ አበባን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል የማድረግ ውጥን ይዞ እየሰራ ነው ፤ ሃላፊው ለዚህ ደግሞ እንደ ኑቢራ ያሉ የግል ተቋማት የተሻሉ የህክምና መሳሪያዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶች የመስጠት እድላቸውን ተጠቅመው የህክምና ቱሪዝምን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

በተጨማሪም መስሪያቤታቸው በመጪዎቹ ጊዜያት የጤና መድህን አሰራርን በማስፋት ከመንግስት የጤና ተቋማት በተጨማሪ የግሎቹም የጤና ተቋማት ለማህበረሰቡ የጤና መድህን አገልግሎቶችን  እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

ኑቢራ የህክምና ማዕከል በ30 ሚሊየን ብር ኢንቨስትመንት የተቋቋመ ሲሆን ለጣፎ አያት፣ 49 አራብሳ፣ 72 ጎሮና ሰሚት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች እሩቅ ሳይጓዙ በርካታ የህክምና አገልግሎቶችና የምርመራ አይነቶችን እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን የማእከሉ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ይበልጣል ሃይማኖት ተናግረዋል።

ደረጃቸውን የጠበቁ ከ30 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎች፤ በአንድ ግዜ ሶስት የተለያዩ ኦፕሬሽን የሚሰጡ የኦፕሬሽን ክፍሎችን (የቀዶ ህክምና) ያካትታል።

የህክምና ማዕከሉ ከ40 በላይ በሆኑ ስፔሻሊስትና ሰብ ስፕሻሊስት ሀኪሞች የተቋቋመ በመሆንና የጤና ሚኒስቴር ተደረገልን ያሉት ድጋድም ዋና ስራ አስኪያጁ ጠቅሰዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ተመርቆ በይፋ ስራውን የጀመረው የህክምና ማዕከሉ ለ100 ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል ተብሏል።

ሚኒስትር ዴኢታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የእናቶችና የሕፃናት የህክምና አገልግሎት ከዚህም በላይ እንዲሰፋ  በመንግሥት በኩል ይፈለጋል፤የጨቅላ ሕፃናት ሕክምና፣ የእናቶች ክትትል፣ የወሊድ አገልግሎት፣ የኦፕሬሽን አገልግሎት ክፍሎቹ የተደራጁበት መንገድ በማዕከሉ ትኩረት እንደሰጠው የሚያሳይ ነው፤ ይህንን ማዕከል ጨምሮ ሌሉቹንም የግል ተቋማት ለማገዝ ሚኒስቴሩ ሁሌም ዝግጁ ነው ብለዋል።

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ፓኪስታን ትክክለኛ አስታራቂ አይደለችም” ኢራን!

የኢራን ህግ አውጪ ኢብራሂም ሬዛኢ ከአሜሪካ ጋር እየተካሄደ ባለው...

በዋይት ሐውስ ዘጋቢዎች የእራት ግብዣ ላይ ስለነበረው ተኩስ የማናውቃቸው ጉዳዮች

ምንም እንኳ ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሐውስ በነበረው የእራት ግብዣ...

ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ! አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

ትግስት አሰፋ ሪከርድ በማሻሻል አሸነፈች !

የ2026 የለንደን ማራቶን ውድድር ሲካሄድ በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት...