ፊንቴክ 250 መኪኖችን ለደንበኞች አስረከበ

Date:

ከወለድ ነፃ የ50% (የሃምሳ ከመቶ) የብድር አገልግሎት

ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ኃ/የተ/የግል ማህበር ለ250 ደንበኞች የኤሌክትሪክ የቢዋይዲ መኪኖችን ዛሬ ሰኔ17/2017ዓ.ም.በመስቀል አደባባይ በተከናወነ ደማቅ ዝግጅት ለደንበኞች አስረከበ!

ይህ መርሐ ግብር 20 ሺህ ኤሌክትሪክ መኪኖችን የመገጣጠም እና የማቅረብ ፕሮጀክት አካል እንደሆነ ነው የተገለጸው።

ፊንቴክ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማቅረቡ ኢትዮጵያ ለምትከተለው አረንጓዴ ኢኮኖሚ አጋዥ ይሆናል ተብሏል።

የኤሌክትሪክ መኪኖችን በ10 ዓመት ውስጥ ከ500 ሺህ በላይ ለማድረስ እየተሰራ እንደሆነ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርሆ ሀሰን ተናግረዋል።

ፊንቴክ ኢንቨስትመንት በየ120 ኪሎ ሜትሩ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ መሙያ ጣቢያዎችን ለመገንባት ማቀዱ በዝግጅት ስነስርዓቱ ላይ ተብራርቷል።

ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ከቢዋይዲ ኩባንያ “Ocean Network” የኤለክትሪክ መኪኖችን ገዝቶ ከ950 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ5 ዓመት የሚከፈል ከወለድ ነፃ የ50% (የሃምሳ ከመቶ) የብድር አገልግሎት አዘጋጅቶ ከ8 ዓመት ዋስትና ጋር በማቅረብ እንቅስቃሴ ላይ ነበር።

ድርጅቱ ቀደም ሲል በኦሮሚያ ባህል ማእከል፣ በስካይ ላይት ሆቴል እና በወዳጅነት ፓርክ እስከ 250 የኤለክትሪክ መኪኖች ለደንበኞች አስረክቧል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...