ፒኤስጂ ሻምፒዮን ኾነ

Date:

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ኢንተር ሚላንን 5 ለ 0 በኾነ ውጤት በመርታት ሻምፒዮን ኾኗል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ዲዚሬ ዱዌ ሁለት፣ አሽራፍ ሀኪሚ፣ ማዩሉ እና ቅቫራስኬሊያ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ፒኤስጂ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሳካት ችሏል።

ፒኤስጂ በውድድር ዓመቱ የሻምፒየንስ ሊግ፣ የፈረንሳይ ሊግ እና ኩፕ ዴ ፍራንስ ዋንጫ አሳክተዋል።

ይህንንም ተከትሎ ፒኤስጂ የሦስትዮሽ ዋንጫ ማሳካት የቻለ የመጀመሪያው የፈረንሳይ ክለብ በመኾን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቀጥለው በሁለት ክለቦች የሦስትዮሽ ዋንጫ ያሳኩ ሁለተኛው አሰልጣኝ ኾነዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...