ፕሬዝደንት ትራምፕ ከ5 የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር ስብሰባ ሊያደርጉ ነው

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከ5 የአፍሪካ አገራት ጋር ስብሰባ ሊቀመጡ መሆኑን አስታወቁ፡፡ ይህ ስብሰባ በኋይት ሀውስ የሚደረግ ሲሆን ለ2 ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት ማለትም ከጁላይ 9 እስከ 11 ለሚከናወነው ለዚህ ስብሰባ 5 የአፍሪካ አገራት መጥሪያ ተልኮላቸዋል፡፡

እነዚህ አገራትም ሴኔጋል፣ ጋቦን፣ ጊኒ ቢሳኦ፣ ላይቤሪያና ሞሪታኒያ ናቸው፡፡ ፕሬዝደንት ትራምፕ እንደገለፁት ከእነዚህ 5 የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር የሚያደርጉት ውይይት በንግድ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

አንድ የኋይት ሀውስ ባለስልጣን ሲናገሩ ‹‹ፕሬዝደንት ትራምፕ አሜሪካንና የአፍሪካ አጋሮቻቸውን የሚጠቅም ትልቅ የንግድ እድል በአፍሪካ ውስጥ እንዳለ እምነት ጥለዋል›› ብለዋል፡፡ በዚህ በመጪው ሳምንት በሚከናወነው ስብሰባም ከ5ቱ የአፍሪካ መሪዎች ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህ አገራት ለምን ተመረጡ የሚለው ጥያቄ የብዙዎች መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ እኚህ የኋይት ሀውስ ባለስልጣን እንዳስረዱት እነዚህ 5 አገራት ከአሜሪካ ጋር የንግድ ስምምነት የፈፀሙ ናቸው፡፡ ፕሬዝደንት ትራምፕ በቅርቡ በመላው አለም የሚገኙ አገራት ላይ የንግድ ታሪፍ ጥለው እንደራደርና እንስማማ ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሰጠው መግለጫ አሜሪካ ከዚህ በኋላ የምትሰጠውን የውጭ እርዳታ በከፍተኛ ሁኔታ እንደምትቀንስ አስታውቋል፡፡ መስሪያ ቤቱ እንዳለው ከዚህ በኋላ አሜሪካ በንግድ ላይ የተመሰረተ የእርዳታ ስራዎች ላይ ትሰማራለች፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኖ ሞር’ ቴአትር በአሜሪካ ለታዳሚ ሊቀርብ ነው

በአገር ውስጥ መድረኮች በነበረው ቆይታ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው...

የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የዘርፉን ተዓማኒነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገለጸ

​​በኢትዮጵያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የሪል ስቴት አልሚዎች እንዳሉ...

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት 54 ‹‹አስገዳጅ›› ህጎችን አፀደቀ

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የደረጃዎች ቦርድ ባካሄደው 5ኛው መደበኛ ስብሰባው፤...

የአዲስ አበባ ቻምበር የንግድ ትርኢት ማካሄድ ጀመረ

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 27ተኛውን አለማቀፍ...