ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሚካሔደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት ካርድ የወሰዱ መራጮች በቂ የመራጭነት ግንዛቤ እንዲኖራቸው 12 መገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም እና በዋና ዋና አደባባዮች በመንቀሳቀስ የመራጮች ትምህርት እየተሰጠ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ሕብረት ለምርጫ አስታውቋል።
የሕብረቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ኃይለማርያም እንደገለጹት፦
መራጮች በምርጫው ወቅት ማድረግ ያለባቸውን እና የሌለባቸውን ድርጊቶች በመግለጽ ትምህርት በመስጠት ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የመራጮች ትምህርት እየተሰጠባቸው ከሚገኙ 12 የብዙኃን መገናኛ አውታሮች መካከል አስሩ የክልል መገናኛ ብዙኃን ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሀገር አቀፍ ተደራሽነት ያላቸው ናቸው ተብሏል።
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙት 10 መገናኛ ብዙኃን የመራጮች ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኙት ሚድያዎች እንደሚገኙበት ክልል በተለያዩ ቋንቋዎች መራጮችን የማንቃት ስራ እየሰሩ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ ሀገር አቀፍ ተደራሽነት ያላቸው ናቸው ተብሏል።
ከመደበኛ መገናኛ ብዙኃን በተጨማሪ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች በምርጫ ወቅት የተከለከሉ ሕጎችን የማሳወቅ ስራ ተሰርቷል ተብሏል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እና በስኬት እንዲጠናቀቅ 14 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በቅንጅት እየሰሩ እንደሆነ የሕብረቱ ዋና ዳይሬክተር አብራርተዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
