የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከ 2 ሰዓት በላይ የፈጀ የስልክ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ላይ ትራምፕ ተኩስ አቁም ላይ መድረስ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት ያነሱ ሲሆን፤ ፑቲን በበኩላቸው ከዩክሬን ጋር ተኩስ ማቆም የሚቻለው ተገቢ ስምምነቶች ላይ ስንደርስ ብቻ ነው ብለዋል።
በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሚደረጉ ድርድሮች የተኩስ አቁምን እና ሌሎች የስምምነት መርሆዎችን ሊያካትቱ ይችላሉም ነው ያሉት።
ሩሲያ እና ዩክሬን የሚያግባቡ ነጥቦች ላይ መድረስ እንዳለባቸውም አንስተው፤ በኢስታንቡል ድርድሩ በድጋሚ መጀመሩ ሁለቱ አካላት በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናቸውን ያሳይልም ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር የተደረገውን ውይይት አድንቀው ገንቢ መሆኑን እንደጠቀሱ ታስ ዘግቧል።
