Date:

ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ!

አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ፣ መላው የስፖርት ቤተሰብ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የከተማው ደርቢ ተጠናቀቀ።

በታላቁ የአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ግዙፎች ፍልሚያ፣ የኢትዮጵያ ቡናን የላቀ የበላይነት ባሳየ መልኩ በኢትዮጵያ ቡና 3 – 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በጨዋታው ኢትዮጵያ ቡና በወጣትና ፈጣን የቡድን ስብስቡ በመታገዝ የጨዋታውን ብልጫ በመውሰድ ነጥቡን ማሳካት ችሏል።

የግብ አግቢዎች፤ ለኢትዮጵያ ቡና፡- ኦካይ ጁል፣ ቢኒያም ጌታቸው እና ዘላለም አባተ

ለቅዱስ ጊዮርጊስ፡- ፍፁም ጥላሁን

በዛሬው ዕለት የሸገርን አውራ ጎዳናዎች በቡናማ እና አረንጓዴ/ቢጫ ቀለም በድምቀት ያጥለቀለቁት ደጋፊዎች፣ ጨዋታው ከሶስት ነጥብ በላይ የክብርና የኩራት ፍልሚያ መሆኑን ዳግም አስመስክረዋል።

ቡናማዎቹ በታክቲክ ብልጫና በቁርጠኝነት ያሳዩት ብቃት ውጤቱን እንዲቀዳጁ አድርጓቸዋል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...