የምግብና መጠጥ ግብዓቶች ቴክኖሎጂና የፕላስቲክ ውጤቶች ለዕይታ የሚቀርቡበት 7ኛውዓለም አቀፍ የአግሮ ፉድ እና ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጵያ የንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
ፕራና ኢቨንትስ ከጀርመን አጋሩ ፌርትሬድ ጋር በመተባበር 7ኛውን “አግሮ ፉድ እና ፕላስት
ፕሪንትፓክ ኢትዮጵያ” ዓመታዊ የንግድ ትርዒት ያዘጋጁት ሲሆን፥ ከመጪው ሰኔ 12 እስከሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ታውቋል።
የንግድ ትርዒቱ ዓለም ዓቀፍ የግብርና፣ የምግብና መጠጥ ግብዓቶች እና ቴክኖሎጂ፥ እንዲሁም የፕላስቲክ፣
የህትመትና የማሸጊያ ቴክኖሎጂና ምርቶችን ያካተተ ነው ተብሏል።
ለሦስት ቀናት በሚቆየው የንግድ ትርዒት ላይ ከ14 ሀገራት የተውጣጡ ከ140 በላይ አውደ ርዕይ አቅራቢዎች ለኢትዮጵያ ገበያ የሚስማሙ ምርቶችንና መፍትሄዎችን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከኦስትሪያ፣ ቻይና፣ ዴንማርክ፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ ጣሊያን፣ ዮርዳኖስ፣ኬንያ፣ ፖላንድ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ታይዋን፣ ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የተውጣጡ ከ130
በላይ ድርጅቶች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።
እነዚህ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ገበያ ተብለው የተዘጋጁ ምርቶችን እና አገልግሎታቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ መጠጥ አምራቾች ኢንዱስትሪ ማህበር የሚዘጋጁ
የውይይት መድረኮች እንደሚካሄዱም ተመላክቷል።
@Arada_Fm
