70 በመቶ ያህል ከውጪ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ጥገኝነት ተላቅቄያለሁ

Date:

የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ በማቅረብ የሚታወቀው ሜሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ  ከውጪ ድርጅቶች የሚያገኘውን የገንዘብ ድጋፍ ለመቀነስ የቢዝነስ ሞዴልን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የሜሪ ስቶፕስ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ዶክተር አበበ ሽብሩ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የእናቶችን፣ የህፃናትን፣ የወጣቶች እና የአፍላ ወጣቶችን  ጤና ለማረጋገጥ ተቋሙ ላለፉት 35 ዓመታት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም እስከ ፈረንጆቹ 2000 ዓመት ድረስ ከአሜሪካ እና ከእንግሊዝ መንግስታት እንዲሁም ከለጋሽ ድርጅቶች በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ይህን አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል።

አሁን ላይ የምእራባውያን ሀገራት  ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እያደረጉት ያለው የገንዘብ ድጋፍ  በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱን ዶክተር አበበ ተናግረው ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት የሚከናወነው ከውጪ ሀገራት በሚገኝ ድጋፍ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ ድጋፍ በአሁኑ ወቅት በተመሳሳይ መልኩ እየቀነሰ መምጣቱን የጠቀሱት ካንትሪ ዳይሬክተሩ እንዲህ ያሉ አገልግሎቶችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ በኩል የሀብት ውስንነቶች እንዳሉ ጠቁመዋል።

በዚህ ወቅት ተቋሙ ራሱን የሚያጠናክርበትን የቢዝነስ ሞዴል ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ከመንግስት የጤና ተቋማት ከፍ ያለ፣ከግል የጤና ተቋማት ባነሰ ክፍያ  አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል።

በዚህም የተነሳ በለጋሽ ድርጅቶች በኩል የሚስተዋለውን የገንዘብ ድጋፍ ስጋቶች መቀነስ መቻሉን የተናገረው ሜሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ  በፈረንጆቹ 2025 በ70 በመቶ ያህል እራሱን ከውጪ ሀገራት ድጋፍ ጥገኝነት ማላቀቁን አስታውቋል።

እንደዚሁም ተቋሙ 80 በመቶ የሚሆነውን አገልግሎቱን ከውጪ ድርጅቶች በሚያገኘው ድጋፍ በገጠሩ የኢትዮጵያ ቦታዎች ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በነፃ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...