የአሜሪካ ጦር በደቡባዊ ኢራን አዲስ ጥቃት ሰንዝሯል።
አሜሪካ የሚሳኤል ይዞታዎችን እና ፈንጂ ውሃ ውስጥ ሊያጠምዱ ሲሞክሩ የነበሩ መርከቦችን ዒላማ ማድረጓን አሳውቃለች።
እርምጃ የወሰድንው ራስን ለመከላከል ነው በሚልም ማዕከላዊ ዕዙ ለማስተባበል ሞክሯል።
የኢራን ሀይሎች ስጋት መደቀናቸውን ተከትሎ የተፈፀመ ጥቃት ነው ሴንት ኮም ቢለውም ድርድሩን ጫና ውስጥ ያስገባዋል ተብሏል።
የኢራን ፖለቲከኞች ድርድሮች በበጎ እየቀጠሉ ነው ባሉበት ሰዓት የተሰነዘረ ጥቃት በመሆኑ ቴህራንም ተመሳሳይ እርምጃ ልትወስድ ትችላለች የሚል ስጋት ተጋርጧል።
እንደ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ጥቃቱ በባንዳር አባስ አቅራቢያ ተፈፅሟል።
በሌላ በኩል በሊባኖሱ ሄዝቦላህ ላይ የእስራኤል ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ማሳወቃቸው ውጥረቱ አደገኛ እየሆነ መምጣቱን ይጠቁማል ተብሏል።
ዜናው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረሰ ከኢራን በኩል የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩም ተዘግቧል።
ኒው ዮርክ ታይምስና አልጀዚራ እንዳስነበቡት።
