75% የአዲስ አበባ ነጋዴዎች የሂሳብ መዝገብ ተቀባይነት አላገኘም

Date:

75 በመቶ የሚሆኑ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ ደረጃውን ያልጠበቀ እና በሙያ ብቃት በሌላቸው ሰዎች የሚዘጋጅ በመሆኑ ተቀባይነት አላገኘም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል ።

ቢሮው ከአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና ከነጋዴ ተወካዮች ጋር ባደረገው ውይይት፣ በጥቅምት ወር በተካሄደው ቅድመ ኦዲት 25 በመቶ ያህሉ ነጋዴዎች ብቻ የሂሳብ መዝገባቸው ተቀባይነት ማግኘቱን አረጋግጧል።

የተቋሙ ኃላፊ ቢኒያም ምክሩ እንደገለጹት፣ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ በባንክ ሂሳባቸው ከሚንቀሳቀሰው ገንዘብ ጋር የማይጣጣም ነው። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በባንክ አካውንታቸው ላይ ቢታይም፣ በሂሳብ መዝገባቸው ላይ ምንም ትርፍ እንዳላገኙ ያሳያሉ።

አንዳንዶቹ ደግሞ ገንዘቡን በህጋዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ወጪ አድርገው ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም የተባለ ሲሆን የሚመጣው የሂሳብ መዝገብ ፕሮፌሽናል ባልሆኑ ሰዎች እየተዘጋጀ ነጋዴው ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑም ተገልጿል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...