የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በጅቡቲ ተሸለመ

Date:

የጅቡቲ ትራንዚተርስ አሶሴሽን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ (ኢባትሎ) በሎጂስቲክስ ዘርፍ ላበረከተው ዓይነተኛ አስተዋጽኦ እና አጋርነት ሽልማት ማበርከቱ ተነግሯል ።

ትናንት በጅቡቲ አምባሳደሮችና የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተደረገው የዕውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ ማህበሩ ላለፉት ዓመታት በነበረን የአብሮነት ጉዞ በስራ አጋርነት ላሳያችሁት ድንቅ ብቃትና ዘላቂ ወዳጅነት ለኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ያለንን ክብር እንገልፃለን ሲል ሸልማቱን መስጠቱን ነዉ የተገለጸው ።

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) እንደተናገሩት በሎጂስቲክስ ዘርፍ ባለን የጋራ ስራ የጭነት ምጣኔን ከፍታ በማረጋገጥና ገቢያችንን በማሳደግ፣ ግንኙነታችንን በማጠናከር፣ የስራ ፈጠራን በማስፋት፣ የሰራተኞቻችንን ጤናማነት በማረጋገጥ ለጠንካራ የኢኮኖሚ ግንባታ መረጋገጥ እና የሁለትዮሽ ተጠቃሚነት እናውለዋለን ብለዋል፡፡

ይህ ሽልማት የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት በክልሉ የሎጂስቲክስ ዘርፍ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ የሚያሳይ ሲሆን፣ የሁለቱ አገራት የትብብር ግንኙነት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...