በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 8ኛው ዓለም አቀፍ የከተሞች እና ሰርኩላር ኢኮኖሚ የትብብር ፎረም ላይ፣ በአፍሪካ እየጨመረ የመጣውን የደረቅ ቆሻሻ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ ውይይቶች ተጀመሩ።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ለሊሴ ነሜ፣ ኢትዮጵያ ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ባሻገር ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ብሔራዊ የሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅታ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።
የከተማና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ድኤታ አቶ ፋንታ ደጀኔ በበኩላቸው፣ ቆሻሻን ወደ ሀብት በመቀየር ዘላቂ የከተማ እድገትን ለማረጋገጥ የታቀዱ ስራዎችን አብራርተዋል።
በጉባኤው ላይ የህንድ አምባሳደር እና የሳይንስና አካባቢ ጥናት ማዕከል (CSE) ዳይሬክተር ዶ/ር ሱንታ ናራእን የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የህዝብ ግንዛቤ ወሳኝ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከCSE ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
