የቻይና እና የሰሜን ኮሪያ የባቡር መስመር ዳግም ተከፈተ

Date:

ለስድስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የቻይና እና የሰሜን ኮሪያ የባቡር ትራንስፖርት ዳግመኛ መጀመሩን ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ መያዙ ተነገረ።

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ይህ የባቡር መስመር፣ ከነገ ጀምሮ በሳምንት ለአራት ቀናት ከቤጂንግ ወደ ፒዮንግያንግ መደበኛ ጉዞውን እንደሚጀምር የቻይና ባቡር ባለሥልጣን አስታውቋል።

ምንም እንኳ ቻይና ከወረርሽኙ ማግስት በፍጥነት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ብትመለስም፣ ሰሜን ኮሪያ ጥብቅ የድንበር ገደቦችን ለማላላት ረጅም ጊዜ ወስዶባታል።

በአሁኑ ወቅት ጉዞው የተፈቀደላቸው ቪዛ ያላቸው ጥቂት የውጭ አገር ዜጎች፣ በሰሜን ኮሪያ የሚኖሩ ወይም የሚማሩ ቻይናውያን ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

የጉዞ ወኪሎች ለነጋዴዎችና ለቱሪስቶች የሚሆን በቂ ትኬት እስካሁን ይፋ እንዳልተደረገ ቢጠቁሙም፣ የትራንስፖርት አገልግሎቱ መጀመር የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ወዳጅነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...