የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺን ጋር በነበራቸው ውይይት በኢራን ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት መሰረትም ሆነ ምክንያት የለውም ብለዋል።
ሩሲያ ለኢራን ሕዝብ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት ታደርጋለች ሲሉ ፑቲን አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል ብሏል ስፑትኒክ።
ቴህራን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚወስዱት እርምጃ ሕጋዊ እንዳልሆነ እና የመከላከል መብት እንዳላት ታስገነዝባለች ሲሉ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ ተናግረዋል።
እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ባደረሱት ጥቃት በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት እየጨመረ መምጣቱን አራጋቺ ጨምረው ገልፀዋል።
ቀደም ብሉ በወጣ ዘገባ ሩሲያ ለኢራን የምትሰጠው ድጋፍ በቴህራን ፍላጎት ላይ እንደሚወሰን ክሬምሊ ማስታወቁን አስነብቧል፡፡
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የፈጸመችውን ጥቃት አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፤ ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ በአዲስ መልክ እየተባባሰ በመጣው ቀውስ ጥልቅ ሐዘን እንደሚሰማት ገልጸዋል።
