ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት እንዳትፈጽም አስጠነቀቁ

Date:

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማኅበራዊ ትስስር መድረካቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም የለባትም በማለት ማስጠንቀቂያ አስተላለፉ።

ፕሬዝዳንቱ ትሩዝ በተባለው የራሳቸው ማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ “እስራኤል፤ እነዚያን ቦምቦች አትጣይ። በጥቃቱ የምትቀጥይ ከሆነ ከፍተኛ ጥሰት ነው። [የጦር አውሮፕላን] አብራሪዎችሽን አሁኑኑ ወደ ቤታቸው መልሺ!” ብለዋል።

ይህ የፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ የመጣው ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የተኩስ አቁም በኢራን እና በእስራኤል መካከል መደረጉን ካስታወቁ በኋላ ነው። እስራኤል በትራምፕ ሃሳብ መስማማቷን ስታሳውቅ፣ ኢራን ደግሞ ጥቃቱን የምታቆመው እስራኤል ካቆመች ብቻ ነው ብላለች።

ነገር ግን ረፋድ ላይ የእስራኤል ጦር ሠራዊት ከኢራን የተወነጨፈ ሚሳዔል አክሽፊያለሁ ቢልም ኢራን ግን ምንም ዓይነት ጥቃት አለመዘንዘሯን አስታውቃለች።

ዶናልድ ትራምፕ ቆየት ብለው ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሁለቱም አገራት የተኩስ አቁሙን ጥሰዋል በሚል ከስሰዋቸዋል።

“ሆን ብለው ማድረጋቸውን እርግጠኛ አይደለሁም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ዛሬ ጠዋት የእስራኤልን ሁኔታ አልወደድኩትም፤ ይህንንም ማስቆም እችል እንደሆነ አያለሁ።”

ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ኢራን “ወደፊት ፈጽሞ ኒውክሌር መሳሪያን አትገነባም” በማለት በኢራን ሁኔታም ደስተኛ አለመሆናቸውን አመልክተዋል።BBC Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...