የኢትዮጵያ ኮንትራክተሮች ማህበር ፕሬዘዳንት ኢንጂነር የሱፍ መሀመድ የአፍሪካ ኮንትራክተሮች ፌዴሬሽን የስራ አመራር አባል ሆነው ተመረጡ።
የኢትዮጵያ ኮንትራክተሮች ማህበር በግብፅ ካይሮ በሚካሄደው 20ኛው የአፍሪካ ኮንትራክተሮች አሶሴሽን እየተሳተፈ ይገኛል።
የ ኢትዮጲያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ኢ/ር የሱፍ መሐመድ በግብጽ ካይሮ እየተካሄደ በሚገኘው 20 ኛው የአፍሪካ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበራት ፌዴሬሽን(AFCCA) ጉባኤ ላይ ም /ፕሬዘዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
በአፍሪካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀገራችን ተቋራጮች እና ባለሙያዎች በስራዎች በሰፊው የመሳተፍ ሙከራዎችን የበለጠ ለማሣደግ ኢ/ር ዩሱፍ መሀመድ ም/ፕሬዘዳንት ሆነው መመረጣቸው እንደ ትልቅ አጋጣሚ የሚወሰድ ይሆናል። ይህ ምርጫም ማህበሩ ለሚያደርገው ሁለንተናዊ እቅድ ደግሞ የሞራል እገዛ እንደሚሆን ታምኖበታል።
